ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ።

0
303

ባሕር ዳር: ግንቦት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሳውዲ ፕሮ ሊግ በአንድ የውድድር ዓመት በርካታ ግቦችን በማስቆጠር አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። በሳውዲ አረቢያ በሳውዲ ፕሮ ሊግ ለአል ናስር እየተጫወተ የሚገኘው ኮከቡ በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ በሊጉ ታሪክ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። በ31 የሊግ ጨዋታዎች 35 ግቦችን ያስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ግቦችን በማስቆጠር አዲስ ክብረ ወሰን ጽፏል። ሮናልዶ በሊጉ 11 ለግብ የሚኾኑ ኳሶችንም አመቻችቶ አቀብሏል።

በ2018/19 አብድረዛቅ ሀምደላህ በሊጉ 34 ግቦችን በማስቆጠሩ የሊጉ ክብረ ወሰን ኾኖ ቆይቷል። “ቁጥሮች ይከተሉኛል እንጂ አልከተላቸውም” የሚለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሊጉን ክብረ ወሰን አሻሽሎታል። በሳውዲ ፕሮ ሊግ ክብረ ወሰን በመስበር የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ኾኖ የጨረሰው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአራት የተለያዩ ሊጎች ላይ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ኾኖ በመጨረስም በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ኾኗል። ሮናልዶ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ፣ በስፔን ላሊጋ፣ በጣልያን ሲሪኤ እና በሳውዲ ፕሮ ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ በመኾን የወርቅ ጫማ ወስዷል።

የ39 ዓመቱ ኮከብ “እድሜ ቁጥር ነው” እያለ ታሪክ እየሠራ መቀጠሉን ቢቢሲ፣ ዘ ሰን፣ ጎል አረቢያ እና ሌሎች ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here