ባሕር ዳር: ግንቦት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ከፈረንሳዩ ሞናኮ ዩናይትድን የተቀላቀለው ማርሻል በክለቡ እንደሚደምቅ ተገምቶ ነበር። በመጀመሪያዎቹ ዓመታትም ተስፍ ሰጭ ብቃት አሳይቶ ነበር።
የኋላ ኋላ ግን ተጫዋቹ በተጠበቀው ልክ እድገት ማሳየት ተስኖት ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት አልቻለም ። ተደጋጋሚ ጉዳት እና የግል ህይወትን በአግባቡ መምራት አለመቻል የተጫዋቹ የእግር ኳስ ችሎታ በውጤታማነት እንዳይታጀብ አድርጎታል።
ፈረንሳዊ አጥቂ ዩናይትድን መልቀቁን ሲገልጽ የክለቡን ደጋፊዎች ከልብ አመስግኗል። “ላደረጋችሁልኝ ነገር ከልቤ አመሰግናለሁ፤ መዝሙራችሁ፣ ማበረታቻችሁ እና ፍቅራችሁ ሁሌም በልቤ ይኖራል”ማለቱን ዩሮ ስፖርት አስነብበቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!