ሀገሩን ለመጨረሻ ጊዜ የሚወክለው ኦሊቪየር ጂሩ።

0
240

ባሕር ዳር: ግንቦት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኦሊቪየር ጂሩ ከዩሮ 2024 ዋንጫ በኋላ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ራሱን እንደሚያገል አስታውቋል፡፡ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የምን ጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ኦሊቪየር ጂሩ ለሀገሩ በ131 ጨዋታዎች 57 ግብ ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች ነው፡፡

ተጫዋቹ በ2018 ሩሲያ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ፈረንሳይ የዋንጫ ባለቤት ስትኾን በስድስት ጨዋታዎች ተሰልፎ ብሔራዊ ግዴታውን በብቃት ተወጥቷል፡፡ ኦሊቪየር ጂሩ ለቢቢሲ እንዳለው “ከብሔራዊ ቡድኑ የሚለቀው ለወጣቶች እድሉን ለመልቀቅ ነው” በሚቀጥለው ወር የኤሲ ሚላን ኮንትራቱ የሚያበቃው የ37 ዓመቱ ኦሊቪየር ጂሩ ከአውሮፓ ዋንጫ በኋላ በአሜሪካን ሜጀር ሊግ ለመጫወት መስማማቱም ተነግሯል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here