ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊዋ ስቱሜ አሰፋ ከሰሞኑ ይፋ በኾነው የሴቶች ማራቶን ቡድን አለመካተቷ ጥያቄ አስነስቷል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በማራቶን ዘርፍ አትሌቶችን ለመምረጥ ቢያንስ በሁለት ውድድሮች ያላቸው ሰዓት ታይቷል ብለዋል።
በዚህ መሠረት ስቱሜ አሰፋ መጋቢት/2016 ዓ.ም ባደረገችው ውድድር 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ55 ማይክሮ ሰከንድ ብትገባም ከዚያ ወዲያ የተወዳደረችበት ውድድር አለመኖሩ በቡድኑ ውስጥ እንዳትካተት አድርጓል ብለዋል። በሴቶች ማራቶን ዘርፍ የተመረጡ አትሌቶች በቅርብ ያደረጓቸው ሁለት ውድድሮች ላይ ያስመዘገቡት ሰዓት ውጤት መስፈርት ነበርም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!