የቼልሲው አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በስምምነት ቡድኑን ለቀቁ።

0
210

ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ52 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አሠልጣኝ ፖቸቲኖ በ2023 ነበር ቼልሲን ለማሠልጠን የሁለት ዓመት ውል የፈረሙት። አሠልጣኙ በውድድር ዘመኑ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ቢገቡም ቡድኑ በፕሪምየር ሊጉ ስድስተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ አድርገዋል።

ፖቸቲኖ ቡድኑን መልቀቃቸው እርግጥ ሲኾን ለቼልሲ ባለቤቶች እና ለዳይሬክተሮች “ለነበረኝ ቆይታ አመሠግናለሁ” ብለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። ሰውዬው ሳውዝአምፕተንን፣ ቶትንሃምን ሆትስፐርን እና ፓርምስ ሴንት ዥርሜንን ማሠልጠናቸው አይዘነጋም። አሁን ቼልሲ ከአይፕስዊች ቡድን አሠልጣኝ ኪይራን ማኬና፣ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ሩበን አሞሪም እና ከበርንሌይ ቪንሴንት ኮምፓኒ አንዱን ያስፈርማል እየተባለ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here