ከከፍተኛ ሊግ የወረዱ ቡድኖች ታውቀዋል።

0
267

ባሕር ዳር: ግንቦት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል፡፡ በውጤቱም ቤንች ማጂ ቡና እና ይርጋጨፌ ቡና 1ለ1 ተለያይተዋል፡፡

ሀላባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮን 2ለ 1 አሸንፏል፡፡

ስልጤ ወራቤ ጅማ አባቡናን 7 ለ 0 ረትቷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ሞጆ ከተማ ፣ ጅማ አባ ቡና ፣ ይርጋጨፌ ቡና፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና ጅማ አባጅፋር ወደ አንደኛ ሊግ መውረዳቸው ታውቋል፡፡

በምድብ “ለ” ደግሞ የካ ክፍለ ከተማ ባቱ ከተማን 2ለ1፣ ደሴ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማን 1ለ0 ሲያሸንፉ ሸገር ከተማ ከነገሌ አርሲ አንድ አቻ ተለያተዋል፡፡

በውጤቱ መሠረትም ወሎ ኮምቦልቻ፣ ካፋ ቡና፣ ቢሾፍቱ ከተማ፣ ባቱ ከተማ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወደ አንደኛ ሊጉ መውረዳቸው ተረጋግጧል ሲል ሶከር ኢትዮጵያ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here