ባሕር ዳር: ግንቦት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሪያል ማድሪድ እና የጀርመን ብሄራዊ ቡድን አማካኝ ተጫዋች ቶኒ ክሩስ ከዩሮ 2024 ጨዋታዎች በኋላ ራሱን ከእግር ኳስ ዓለም እንደሚያገል አስታውቋል፡፡ የ34 ዓመቱ ክሩስ በ2014 ከባየርን ሙኒክ ሪያል ማድሪድን በመቀላቀል እስከ 2023/2024 የውድድር ዘመን በ305 ጨዋታዎች ተሰልፎ 22 ግብ በስሙ ማስመዝገብ የቻለ ተጫዋች ነው፡፡
በማድሪድ ስምንት ቁጥር መለያ በመልበስ የሚታወቀው ክሩስ ከቡድኑ ጋር አራት የላሊጋ እና አራት የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል፡፡ ተጫዋቹ ሀገሩ ጀርመን የ2014 የዓለም ዋንጫን ስታሸንፍ የእርሱ ሚና ከፍተኛ እንደነበር የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።
ተዋቂው ዘ ኢንዲፔንዳንት ድረ ገጽ ቶኒ ክሩስን” ከሪያል ማድሪድ ምርጥ አማካዮች መካከል አንዱ ነው” ሲለው፤ ዴይሊ ሜይሊ በበኩል “የመሐል ሜዳ ሞተር ” በማለት አዎድሶታል፡፡ የሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ።ግሞ “ቶኒ ክሩስ በሪያል ማድሪድ ታሪክ ውስጥ ከታላቅ ተጫዋቾች አንዱ ነው” በማለት አሞካሽተውታል፡፡
ጀርመናዊ ክሩስ እግር ኳስን በግሪፍስዎላዴር የወጣት ቡድን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1997 መጫወት ጀምሯል። በባየርን ሙኒክ፣ በባየር ሊቨርኩሰን እና በሪያል ማድሪድ ቡድኖች ተጫውቷል፡፡ ለብሄራዊ ቡድኑ ደግሞ ከ2010 ጀምሮ በ108 ጨዋታዎች ተሰልፎ 17 ግቦችን ማስመዝገብ የቻለ ተጫዋች ነው፡፡ ይህ ድንቅ አማካይ ከቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ በኋላ እግር ኳስ በቃኝ ብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!