የማርኮ ሮይስ ስንበት በሲግናል ኢድና ፓርክ!

0
200

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በቦርሲያ ዶርትመንድ ቤት 12 ዓመታትን ያሳለፈው ጀርመናዊ ሮይስ ለክለቡ የመጨረሻ ጨዋታውን አድርጓል። በወርቃማ የእግር ኳስ ጊዜው በሚያማልል ገንዘብ በትልልቅ ክለቦች ተፈልጎ ታማኝነቱን ለቢጫ እና ጥቁሩ መለያ አድርጓል። በዚህም በምርጦቹ የክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ እጅግ ይወደዳል፣ ይከበራል።

ከ12 ዓመታት ታማኝነት በኋላም ዶርትመንድ የቦንደስ ሊጋ የመጨረሻ ጨዋታውን ሲያደርግ ሮይስ የደመቀ ሽኝት በሲግናል ኢድና ፓርክ ተደርጎለታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here