“ጋርዲዮላ የዓለም ምርጡ አሠልጣኝ ነው” የርገን ክሎፕ

0
270

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የርገን ክሎፕ ባለፉት ዓመታት በሊቨርፑል ቤት ድንቅ ሥራን ሠርተዋል። የፕሪምየር ሊጉን የበላይነት የወሰደውን ማንቸስተር ሲቲን የፈተነ የተሻለው ቡድንም ከሞላ ጎድል የእሳቸው ነው። ክሎፕ በቀዮቹ ቤት የሚናፈቅ ትዝታን አኑረው ዛሬ በድምቀት ከክለቡ ይሰናበታሉ። በዚህ ስሜት ውስጥ ኾነው ስለባለፉት ዓመታት ተቀናቃኛቸው ጋርዲዮላ ተጠይቀዋል።

ክሎፕም “ጋርዲዮላ የዓለም ምርጡ አሠልጣኝ ነው” ብለዋል። “ሲቲ ላይ ምንም ጥያቄ ይነሳ ጋርዲዮላ ግን ጋርዲዮላ ነው፤ ማንም አሠልጣኝ ሲቲን ቢይዝ በተከታታይ አራት ዋንጫን ማንሳት ፈጽሞ አይችልም” ሲሉም ጋርዲዮላን አድንቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here