“ያሉንን ሰፊ አቅሞች እና የጋራ የልማት ግቦች ስናጤን ደቡባዊው ዓለም ለደቡብ-ደቡብ የኢኮኖሚ ትብብር መጎልበት ታላቅ አቅም እንዳለው እንረዳለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

15

ባሕር ዳር: ኅዳር 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ያሉንን ሰፊ አቅሞች እና የጋራ የልማት ግቦች ስናጤን ደቡባዊው ዓለም ለደቡብ-ደቡብ የኢኮኖሚ ትብብር መጎልበት ታላቅ አቅም እንዳለው እንረዳለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡

“ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሁለተኛውን የደቡባዊ ዓለም ድምጽ ጉባኤ መክፈቻ የመሪዎች ውይይት መርሐ ግብር ስላካሄዱ አመሠግናቸዋለሁ” ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ።

በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ትብብር የማጠንከርን፣ በአንድ ድምጽ የመናገርን፣ በዓለም የኢኮኖሚ ጉዳዮች የጎላ ሚና መጫወትን እንዲሁም ፈጠራ እና የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ አቅሞችን የመጠቀምን አስፈላጊነት ሃሳብ አካፍያለሁም ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!