“ዩኒቨርሲቲዎቻችን የሕዝባችንን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ መኾን አለባቸው” ፕሬዚደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ

27

ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ)ዩኒቨርሲቲዎቻችን የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ፣ የእርስ በርስ መስተጋብርን የሚያጠናክሩ እና የሀሳብ ልዕልናን የሚያፈልቁ መሆን እንዳለባቸው ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገልጸዋል።

ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምረቃ መርሐ-ግብር ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎችና ለተመራቂ ወላጆች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚዳንቷ ትምህርት መማር ማለት የባህሪ ለውጥ ማምጣት መሆኑንና ራስን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ከተሳሳተ መንገድ መመለስ መሆኑን ተናግረዋል።

የተማረ ሰው የሀገሩን ችግር የሚፈታ እና አድማሱን በማስፋት ውጤታማ ሥራ የሚሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥራት ያለው የሰው ኃይል ለማቅረብ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ስለመሆኑም አንስተዋል።

ፕሬዚዳንቷ ተመራቂ ተማሪዎች በየትኛውም ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ሀገራችሁ ኢትዮጵያን እንደቀደሙት አባቶችና እናቶች እንድትወዱ አሳስባለሁ ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!