የጣና ሞገዶቹ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ድል አደረጉ።

12

ባሕር ዳር: መስከረም 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የጣና ሞገዶቹ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ድል አድርገዋል።

ሀብታሙ ታደሰ በመጀመሪያው አጋማሽ በተጨማሪ ደቂቃ እና በሁለተኛው አጋማሽ በ90ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ባሕርዳር ከተማ ክለብ አፍሪካን መርታት ችለዋል።

ክለብ አፍሪካ በጨዋታው በባሕር ዳር ከተማ የግብ መረብ ላይ ግብ ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል።

የጣና ሞገዶቹ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ ማጣሪያ የታንዛኒያውን አዛም በመርታት ነበር በሁለተኛው ዙር ጨዋታ ከቱኒዚያው ክለብ ክለብ አፍሪካን ጋር የተገናኙት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!