የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የጋራ አጀንዳችን ነው – ምክር ቤቱ

21

ባሕር ዳር: መስከረም 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ፣ የልማትና የሰላም ግንባታ ጉዳይ የጋራ ሀገራዊ አጀንዳችን ሆኖ ይቀጥላል ሲል የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ፡፡ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ እንዳሉት የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነቶች ቢኖሩንም በሀገራዊ ልማት፣ ዘላቂ ሰላምና አንድነታችንን ማስጠበቅ ላይ ልንደራደር አይገባም፡፡

በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ የልማት ዕቅዶች ላይ አጋዦች እንጂ ፈፅሞ የአፍራሽነት ሚና ሊኖረን አይገባም ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡ የቀጣይ ሥራዎቻችን ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባሻገር ለማኅበራዊና የፖለቲካ መስተጋብሮች ቁርኝት ይበልጥ አጋዥ ሆነው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!