ባሕር ዳር: ኅዳር 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ምሽቱን ይካሄዳሉ፡፡ በምድብ ሦስት ሜቄዶንያ ማለፏን ያረጋገጠችውን እንግሊዝን ታስተናግዳለች፡፡ በተመሳሳይ ምድብ ዩክሬን ከጣሊያን ጋር ትጫወታለች፡፡
ምድቡን እንግሊዝ በአሥራ ዘጠኝ ነጥብ ስትመራው ጣሊያን እና ዩክሬን በ13 ነጥብ በግብ ክፍያ ብቻ ተለያይተው ተቀምጠዋል፡፡
በምድብ አምስት የፋሮ ደሴቶች በሜዳዋ ከአልባንያ እንዲሁም ቼክ ሪፐብሊክ ከሞልዶቪያ ጋር ይጫወታሉ፡፡ይህን ምድብ አልባንያ በ14 ነጥብ ስትመራው ቼክ ሪፐብሊክ ደግሞ በ12 ነጥብ በሁለተኛነት ተቀምጣለች፡፡
በምድብ ስምንት ሳን ማሪኖ ከፊንላንድ፣ ስሎቬኒያ ከካዛኪስታን፣ ሰሜን አየር ላንድ ከዴንማርክ የሚገናኙ ይኾናል። ዴንማርክ ምድቡን በ22 ነጥብ ስትመራው ስሎቬኒያ በ19 ነጥብ በሁለተኛነት ትከተላለች፡፡
ዘጋቢ፡- በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!