ባሕር ዳር: ኅዳር 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምድብ ሁለትን የምትመራው ፈረንሳይ ጅብራልተርን ታስተናግዳለች፡፡ በዚሁ ምድብ በሁለተኛነት የምትገኘው ኔዘርላንድስ አየር ላንድን ትገጥማለች፡፡
በምድብ አራት አርሜኒያ ከዌልስ፣ ላቲቪያ ከክሮሽያ ይጫወታሉ፡፡
በምድብ ዘጠኝ የሚገኙት ቤላሩስ ከአንዶራ፣ እስራኤል ከ ሩማኒያ፣ ስዊዘርላንድ ከኮሶቮ ይጫወታሉ፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በትናንት ምሽቱ ጨዋታ ካዛኪስታን ሳን ማሪኖን 3ለ1፣ ፊንላድ ሰሜን አየር ላንድን 4ለ0፣ ዴንማርክ ስሎቪንያን 2ለ1 አሸንፈዋል፡፡
ምድብ አንድን ስፔን፣ ምድብ ሁለትን ፈረንሳይ በተመሳሳይ በ18 ነጥብ ይመሩታል፡፡
ምድብ ሦስትን ደግሞ እንግሊዝ በ19 ነጥብ፣ ምድብ አራትን ቱርክ በ16 ነጥብ፣ ምድብ አምስትን አልባኒያ በ14 ነጥብ እየመሩት ይገኛሉ፡፡
ምድብ ስድስትን ኦስትሪያ በ19 ነጥብ፣ ምድብ ሰባትን ሀንጋሪ በ15 ነጥብ፣ ምድብ ስምንትን ዴንማርክ በ22 ነጥብ፣ ምድብ ዘጠኝን ስዊዘርላንድ በ16 ነጥብ፣ ምድብ 10ን ፖርቱጋል በ27 ነጥብ ይመሩታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዘጋቢ ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!