የሱዳን ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጀኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን አዲስ አበባ ገቡ።

16

ባሕር ዳር: ኅዳር 5/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሱዳን ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጀኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃንን እና ልዑካን ቡድናቸው አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዛሬ የሱዳን ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጀኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃንን እና ልዑካን ቡድናቸውን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በመገኘት ተቀብለዋል::

በመቀጠልም ሁለቱ መሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የጋራ በሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!