ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የ ጄ ኬ ኤስ የካራቴ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።

14

ባሕር ዳር: መስከረም 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የ ጄ ኬ ኤስ (jks) የካራቴ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

በዱባይ እየተካሄደ ባለው የእስያ አፍሪካ ዋንጫ የjks የካራቴ ውድድር ላይ ተሳታፊ የኾኑት ሦስት ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች ሜዳሊያ አግኝተዋል።

በመድረኩ በ60 ኪሎ ግራም የተወዳደረው ናትናኤል በየነ ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያስገኝ በተመሳሳይ ውድድር ኤፍሬም አደም በ84 ኪሎ ግራም እና አስቻለው ክብሩ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ኾነዋል።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው በውድድሩ ከ29 ሀገራት የተውጣጡ ስፖርተኞች እየተሳተፉበት ይገኛል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!