አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።

116

ባሕርዳር፡ ጥር 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ጋር ተወያዩ፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሰዓታት በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሀገራቱ መካከል ስላለው ስትራቴጂያዊ ትብብርና በባለብዙ ወገን ትብብር ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት አድርገዋል፡፡

በቅርቡ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ቺን ጋንግ የአምስት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝትን ዛሬ በኢትዮጵያ መጀመራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!