መስከረም: 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አርቢትር ባምላክ ተሰማ የ2024 በኮቲዲቯር የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ በዋና ዳኝነት ለመምራት ተመርጠዋል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የኮትዲቯሩን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞችን ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ነው ኢትዮጵያዊውን ዓለም አቀፍ ዳኛ አንደኛው አድርጎ ያካተታቸው።
ካፍ የመሀል እና ረዳት ዳኞች፣ የቪዲዮ ረዳት ዳኞች፣ ቴከኒካል ኢንስትራክተሮች፣ የቫር (VAR) ቴክኒሻኖች እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ባለሙያዎችም በዝርዝሩ አካቶ አውጥቷል።
85 ባለሙያዎች ይፋ በሆኑበት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የአፍሪካ ዋንጫን ከሚመሩ ዳኞች አንደኛው ሆነው ተካተዋል።
በዝርዝሩ ከ26 ሀገራት 32 ዋና ዳኞች የተመረጡ ሲኾን፥ አርቢትር ባምላክ ተሰማ ኢትዮጵያን ወክለው በዝርዝሩ መካተታቸውን ካፍ አስታወቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!