ባሕር ዳር: ኅዳር 7/2016 ዓ.ም በፓሪስ የኦሎምፒክ ውድድር ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የመለማመጃ ስታዲየም ፈቃድ የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል። ስምምነቱ የተፈረመው በፓሪሱ አንቶኒ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን ስታዲየም ለመጠቀም ነው፡፡
በሐምሌ ወር ለሚጀምረው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የአትሌቲክስ ቡድኑ ለሚያደርገው ልምምድ የሜዳ ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና የአንቶኒ ክፍለ ከተማ ከንቲባ ዣን-ኢቭ ሶናሌ ናቸው።
በተያያዘ ዜና የፓሪሱ ኦሎምፒክ በፈረንሳይ እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለቡድኑ አቀባበል ለማድረግ የሚያስችል ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
ዘጋቢ:- በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!