በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሞቃዲሾ ገባ።

38

ባሕር ዳር: ጳጉሜን 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሶማሊያ ሞቃዲሾ ገብቷል።

ልዑኩ ሶማሊያ ሞቃዲሾ የተገኘው በመጀመሪያው የኢትዮ-ሶማሊያ የጋራ ሚኒስትር ኮሚሽን ጉባዔ ለመሳተፍ እንደሆነ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኤደን አዴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሶማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሣላህ አሕመድ ጃማ እና በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሃመድ ተቀብለዋቸዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!