ባሕር ዳር: ኅዳር 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጦፋ መሐመድ ዛሬ ጥዋት ወደ ኮምቦልቻ ከተማ ገብተዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን፣ የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊው ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ውኃ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ.ር) ፣የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አቶ መሐመድአሚን የሱፍ እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!